ለልደታ ክ/ከተማ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት በተደጋጋሚ የሚቀርቡ የአገልግሎት ጥያቄዎች

የነዋሪነት ተመዝጋቢዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  1. ከሌላ የመኖሪያ ቦታ የመጣ ከሆነ ይኖርበት ከነበረው ቦታ ህጋዊ መልቀቂያ ማቅረብ አለበት፤
  2. መደበኛ የመኖሪያ ቦታ ያለው ወይም በሚመዘገብበት ቦታ በነዋሪነት የተመዘገበ አስመዝጋቢ ነዋሪ ማቅረብ መቻል ያለበት ሲሆን መልቀቂያዉ በአስመዝጋቢው ማህደር ዉስጥ መመዝገብ እና መያያዝ አለበት፤
  3. ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዉጭ የሚኖርና መልቀቂያ ይዞ በመምጣት በነዋሪነት ለመመዝገብ ጥያቄ የሚያቀርብ ግለሰብ ጥያቄ ካቀረበበት ቀን ጀምሮ ለሶስት ወር እና ከዛ በላይ በከተማ ውስጥ መቆየት አለበት፤
  4. ከላይ በ (ሐ) የተደነገገዉ እንደተጠበቀ ሆኖ ከአቅም በላይ በሆነ ህመም ምክንያት፣ በትምህርት፣ በመንግስት የስራ ኃሊፊነት ዝዉዉር፣ ከሁለት አንዳቸዉ የትዳር አጋር በከተማዉ ነዋሪነት ተመዝግበዉ ያለ ተጋቢዎች ጥያቄ ሲያቀርቡ በማስረጃ በማረጋገጥ ተመዝጋቢዎቹ ሶስት ወር በከተማዉ መጠበቅ ሳይጠበቅባቸዉ በወረዳ ስራ-አስኪያጅ እየተረጋገጠ በነዋሪነት እንዳመዘገቡ ሊፈቅድ ይችላል፤
  5. በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ (ሐ) የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ መልቀቂያ ማስረጃውን ለወረዳ ጽህፈት ቤት ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ በቋሚነት ለመመዝገብ እየጠበቀ መሆኑን የሚገልጽ ለሶስት ወራት ያህል የሚያገለግለ የደብዳቤ ማስረጃ ይሰጠዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ ይህን ያውቁ ኖሯል? ይጫኑ።

ስለ መታወቂያ አሰጣጥ

  1. መታወቂያ ኢትዮጵያዊ የከተማዉ ነዋሪ ለሆነ ተመዝጋቢ ብቻ በካርድ ወይም በሌሎች የቴክኖልጂ አማራጮች የሚሰጥ የነዋሪነት ማረገጋጫ ነዉ፤
  2. ዕዴሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በሊይ የሆነው ኢትዮጵያዊ በሚኖርበት ወረዳ በነዋሪነት የተመዘገበ ሰው ስለማንነቱ የሚገልጽ መታወቂያ እንዲሰጠው የመጠየቅ መብት አለው፤
  3. በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ (2) መሠረት ጥያቄ የሚያቀርብ ሰው በወረዳው ጽ/ቤት በአካሌ ቀርቦ ከ6 ወር ወዲህ የተነሳውን 2 ጉርድ ፍቶግራፍ በመያዝና የተዘጋጀውን አገልግሎት መጠየቂያ ቅፅ በመሙላት አገልግሎቱን ያገኛል፤
  4. መታወቂያ በውክልና አይሰጥም፤ አይታደስም፤
  5. መታወቂያ የተሰጠው ነዋሪ መታወቂያው የሚያስገኘውን መብትና ጥቅም ያገኛል፤
  6. በነዋሪነት ተመዘግቦ በውጭ ሀገር ሲኖር የነበረ ዜግነቱን ያልቀየረ ኢትዮጵያዊ በዚህ መመሪያ አንቀፅ 12 የተገለፁትን ሲያሟላ መታወቂያ ይሰጠዋል፤
  7. ተመዝጋቢዉ ቀድሞ ከሚኖርበት መልቀቂያ የሚያቀርብ ነዋሪ መታወቂያ በሚጠይቅበት ወረዳ የነዋሪነት ምዝገባ ቅፅ ውስጥ መልቀቂያዉ ለ3 ወራት ተመዝግቦ ከተቀመጠ በኋላ በነዋሪነት ሲመዘገብ መታወቂያ እንዲሰጠው የመጠየቅ መብት አለው፡፡ ጽ/ቤቱ ተመዝጋቢዉ በነዋሪነት ለመመዝገብ የቆይታ ጊዜውን እየጠበቀ መሆኑን የሚገልፅ ማረጋገጫ ማስረጃም በጽ/ቤቱ ህጋዊ ማህተም አረጋግጦ ለተመዝጋቢዉ መስጠት አለበት፤
  8. በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ 7 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በመመሪያው አንቀፅ
  9. መሰረት ተመዝጋቢዎች መልቀቂያቸው ሶስት ወር ሳይጠብቅ በነዋሪነት ተመዝግበዉ መታወቂያ አገልግሎት ያገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ ይህን ያውቁ ኖሯል? ይጫኑ።

ያላገባ/ች/ የምስክር ወረቀት ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

  • አመልካቾች ማንነታቸዉን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የአሽከርካሪነት ፈቃድ ወይም ትራቭል ዶክመንት ወይም የስደተኛ መታወቂያ ኮፒ ማቅረብ አለባቸዉ፤
  • አመልካቾች በአካል ወይም በህጋዊ ወኪል ቀርበዉ አገልግሎት ማግኘት ይችላል፤
  • ከስድስት ወር ወዲህ የተነሱት 4x4 ወይም የፓስፖርት መጠን ጉርድ ፍቶግራፍ ማቅረብ አለባቸዉ፤
  • ጥያቄው የቀረበው በውክልና ከሆነ ተወካይ የወካይ የጋብቻ ሁኔታን የሚገልፅ ማስረጃ እንዲያወጣ መብት የሰጠ መሆኑን በግልጽ የሚጠቅስ ህጋዊነቱ የተረጋገጠ ዉክልና፣ የወካይን ማንነት የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የአሽከርካሪነት ፈቃድ ወይም ትራቭል ዶክመንት ወይም የስደተኛ መታወቂያ ኮፒ ማቅረብ አለበት፤
  • አመልካቾች ከኢትዮጲያ ውጪ የሚኖሩ ኢትዮጲያውያን እና ትውልደ ኢትዮጲያውያን ከሆኑና ጥያቄዉ በዉጭ አገር ዉክልና የቀረበ ሲሆን በውጭ ጉዲይ ሚኒስቴር እና በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ተመዝግቦ የተረጋገጠ መሆን አለበት፤
ለበለጠ መረጃ ይህን ያውቁ ኖሯል? ይጫኑ።

ስለ ያላገባ ማስረጃ አሰጣጥ፣ ይዘት፣ እድሳት እና የመረጃ ማስተካከያ

  • አመልካቾች ጋብቻ ያልፈፀሙ ስለ መሆኑ ከነዋሪነት መመዝገቢያ ቅጽ ወይም ከዲጂታል ምዝገባ ላይ ተረጋግጦ በተጨማሪም ቃለ-መሃላ በመፈፀም አገልግሎት ማግኘት ይችላል፤
  • ያላገባ ማስረጃ የሚያገለግለው ለስድስት ወር ብቻ ሲሆን ለእድሳት ጥያቄ ሲቀርብ አዲስ የምስክር ወረቀት መስጠት ሳያስፈልግ የጋብቻ ሁኔታዉ ያልተቀየረ መሆኑ ከቅጽ ሊይ በመረጋገጥ የሚታደስ ይሆናል፤
  • አመልካቾች ከፍቺ ወይም ከትዳር አጋር ሞት ወይም የመጥፋት ውሳኔ በኋላ የያላገቡ መሆናቸውን ማስረጃ ሲጠይቁ የሞት ኩነት ወይም የፍቺ ምዝገባ ማስረጃ ሲያቀርቡ ማስረጃዉ ከኩነቶቹ ክስተት ግዜ ወዲህ ያላገቡ መሆኑ ቀን፣ ወር እና ዓመተ ምህረት ተጠቅሶ አገልግሎቱ ይሰጣቸዋል፤
  • አመልካቾች ጋብቻ ከፈፀሙ በኋላ ከጋብቻ በፊት ያላገቡ መሆናቸውን ማስረጃ እንዲሰጣቸው ከጠየቁ የጋብቻ ማስረጃቸውን በማቅረብ እና ቃለ-መሃላ በመፈፀም ጋብቻ እስከፈፀሙበት ድረስ ቀን፣ ወር እና ዓመተ ምህረት ተገድቦ አገልግሎቱን ያገኛል፤
  • የነዋሪነት ምዝገባ በሚከናወንበት ወቅት በነዋሪነት ምዝገባ ቅጽ ላይ የሰፈረ የጋብቻ ሁኔታ ስህተት ሆኖ ሲገኝ የተመዘገበውን መረጃ በስህተት መመዝገቡን ጉዳዩን በሚያውቁ በሶስት ሰዎች ሲያረጋግጥ ስለ መረጃዉ ስህተት ቃለ-መሃላ በማስፈፀም ትክክለኛው መረጃ እንዲስተካከል ይደረጋል፤
  • መልቀቂያ አቅርበዉ በነዋሪነት የሚመዘገቡ ነዋሪዎች ስለ ጋብቻ ሁኔታቸው ማስረጃ ሲጠይቁ የሚሰጣቸዉ ማስረጃ በመልቀቂያ ላይ ተመዝግቦ ያለዉ የጋብቻ ሁኔታ ከሆነና የመረጃ ማስተካከያ ጥያቄ ሲያቀርቡ መረጃዉ የሚስተካከለዉ አስቀድሞ ከኖሩበትና መልቀቂያ ከወሰዱበት ቦታ መረጃዉ ታርሞ በደብዳቤ ሲቀርብ ነዉ፡፡
  • ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሰጠዉ የጋብቻ ማስረጃ አመልካቾች በኢትዮጵያ ውስጥ ስለነበራቸው የጋብቻ ሁኔታ ብቻ የሚገልጽ ይሆናል፡፡
  • ያላገባ ማስረጃ ሰርተፍኬት የአመልካቾችን የግል መረጃ እና የጋብቻ ሁኔታ የሚገልጹ መረጃዎችን የሚያካትት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ ይህን ያውቁ ኖሯል? ይጫኑ።