Welcome to Lideta Subcity Civil Registration and Residency Service Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       Baga gara Waajjira Galmee Siivilii fi Tajaajila Jireenyaa Kutaa Magaalaa Lidetaatti Nagaan Dhuftan!

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

የልደታ ክፍለ ከተማ የሲቭል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት የወሣኝ ኩነት ምዝገባና የብሄራዊ መታወቂያ አዋጅ ቁጥር760/2004 እና በተሻሻለው አዋጅ 1049/2009 እና ይሄንን ለማስፈፀም በወጣው በአ/አበባ ከተማ አስተዳደር የወሣኝ ምዝገባ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 63/2007 ለተቋቋሙ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት እየተወጣ ይገኛል፡፡ ጽ/ቤቱ በሲቭል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ዘርፎች ተደራጅቶ ያለ ሲሆን የልደትና፣የሞት፣የጋብቻ፣ የፍቺ የጉዲፈቻ፣ የነዋሪነት መታወቂያ የነዋሪነት አገልግሎት፣ ያላገባ፣ የመሣሰሉትን አገልግሎቶችን ለአገልግሎት ፈላጊው ህብረተሰብ መስጠት ዋንኛው ተግባር ነው፡፡

ለነዋሪውና ለህዝብ አደረጃጀቶች ለባለድርሻ አካላት የሚከሰቱ ኩነቶች በወቅቱ እንዲመዘገቡ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እንዲሰራ ተግባር ነው፡፡ የሚሰጡ የመረጃና ማስረጃ አገልግሎቶችን ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ከማድረግ በተጨማሪ ለነዋሪው በቀላሉ ተደራሽ የሆነ አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ ከምዝገባ የተገኙ መረጃዎችን አደራጅቶ በመያዝ በማህበራዊ በአስተዳደራዊ ለኢኮኖሚያዊና ለተለያዩ ኘሮግራሞች እቅድ ብቁ መረጃ ማቅረብ የተሰጡ ኃላፊነትና... ተጨማሪ ያንብቡ

ወ/ሮ ዘነበች ኢረና , የልደታ ክ/ከተማ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

የልደታ ክ/ከተማ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡