የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

የልደታ ክፍለ ከተማ የሲቭል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት የወሣኝ ኩነት ምዝገባና የብሄራዊ መታወቂያ አዋጅ ቁጥር760/2004 እና በተሻሻለው አዋጅ 1049/2009 እና ይሄንን ለማስፈፀም በወጣው በአ/አበባ ከተማ አስተዳደር የወሣኝ ምዝገባ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 63/2007 ለተቋቋሙ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት እየተወጣ ይገኛል፡፡ ጽ/ቤቱ በሲቭል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ዘርፎች ተደራጅቶ ያለ ሲሆን የልደትና፣የሞት፣የጋብቻ፣ የፍቺ የጉዲፈቻ፣ የነዋሪነት መታወቂያ የነዋሪነት አገልግሎት፣ ያላገባ፣ የመሣሰሉትን አገልግሎቶችን ለአገልግሎት ፈላጊው ህብረተሰብ መስጠት ዋንኛው ተግባር ነው፡፡

ለነዋሪውና ለህዝብ አደረጃጀቶች ለባለድርሻ አካላት የሚከሰቱ ኩነቶች በወቅቱ እንዲመዘገቡ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እንዲሰራ ተግባር ነው፡፡ የሚሰጡ የመረጃና ማስረጃ አገልግሎቶችን ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ከማድረግ በተጨማሪ ለነዋሪው በቀላሉ ተደራሽ የሆነ አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ ከምዝገባ የተገኙ መረጃዎችን አደራጅቶ በመያዝ በማህበራዊ በአስተዳደራዊ ለኢኮኖሚያዊና ለተለያዩ ኘሮግራሞች እቅድ ብቁ መረጃ ማቅረብ የተሰጡ ኃላፊነት

ወ/ሮ ዘነበች ኢረና , የልደታ ክ/ከተማ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ
image description